
በቤትዎ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (EV) ቻርጀር ሲያስገጥሙ ፈፅሞ ሊሰሯቸው የማይገቡ 3 አደገኛ ስህተቶች!
በቤታችን የ32A/7kW AC ቻርጀር ስናስገጥም ፈፅሞ ማድረግ የሌለብንን 3 ዋና ዋና ወሳኝ ስህተቶች በዝርዝር እናያለን። እነዚህን ስህተቶች ካስወገዳችሁ የመኪናችሁን ደህንነት ከመጠበቃችሁም በላይ፤ ቻርጀራችሁን ከጉዳት እና እራሳችሁን ካልተፈለገ ተጨማሪ ወጪ ትጠብቃላችሁ።
1ኛ የቆጣሪውን አቅም(Electric power meter) እና ዋናውን ብሬከር (Main Breaker) ሳያረጋግጡ ዘርጋታ መሥራት፤
ማንኛውም ኦሪጅናል ባለ 32A AC ቻርጀር በሰዓት 7 kilo-watt (7 kW) የኤሌክትሪክ ኃይል የመሳብ አቅም አለው። ይህም ማለት የቤታችሁ ዋና ኤሌክትሪክ ቆጣሪ እና ዋናው ብሬከር ይህንን 32A (7 kW) ኃይል የመሸከም አቅም ሊኖረው ይገባል።
የቆጣሪያችሁ አቅም ከ 7kW በታች እና ዋናው ብሬከር ከ 32A በታች ከሆነ በፍጹም የቻርጀር ዘርጋታ መሥራት የለበትም። ቻርጀ ማድረግ ስትጀምሩ ብሬከሩ ወዲያውኑ ይወርዳል (Trip ያደርጋል)። ስለዚህ ዘርጋታ ከመጀመራችሁ በፊት የቆጣሪያችሁን አቅም ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ባለሙያዎች ጋር ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
2ኛ ለቻርጀሩ የማይሆን ያልተመጣጠነ ብሬከር (Breaker) መጠቀም፤
በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ አብዛኛው የቤት ውስጥ መስመር Single-phase (220V-240V) ነው። ለ 32A AC ቻርጀር ደግሞ ለብቻው የሚገጠም Dedicated Breaker ያስፈልጋል።
- ከ 32A በላይ (50A/63A) መጠቀም፡ መስመር ወይም ቻርጀሩ ላይ ችግር ቢፈጠር ብሬከሩ በጊዜ "ትሪፕ" ስላማያደርግ የቻርጀሩ ቦርድ ሊቃጠል ይችላል።
- ከ 32A በታች (16A/25A) መጠቀም፡ ቻርጀሩ 32A መሳብ ሲጀምር ብሬከሩ ወዲያውኑ እየወረደ ቻርጅ ማድረግ አይፈቅድላችሁም።
ስለዚህ ለ 32A AC ቻርጀር በትክክል 2-Pole 32A Breaker መጠቀም ይኖርብናል።
3ኛ ደረጃውን ያልጠበቀ እና የተሳሳተ የኬብል (Cable) ውፍረት መጠቀም፤
32A ማለት ከፍተኛ ሙቀት የሚፈጥር የኤሌክትሪክ ፍሰት ነው። መኪናችሁ ደግሞ ይህንን ኃይል ከ 6 እስከ 8 ሰዓታት ያላቋረጠ ይስባል።
ለዘርጋታ የምንጠቀመው ኬብል ከዚህ አነስተኛ ሙቀት ይስብና የእሳት ቃጠሎ እንዲፈጠር ያደርጋል። ከ3X6 mm2 ከበለጠ ደግሞ ከመጠን በላይ ኤሌክትሪክ ሀይል በማለፍ የቤት ቆጣሪያችን፣ የመኪናውን ቻርጀርና የመኪናውን Onboard charger (OBC) በቀጥታ እንዲቃጠሉ ያደርጋቸዋል።
ስለዚህ adjustableም ሆነ fixed power ማስተላለፍ ለሚችሉ 32A ቻርጀሮች ግዴታ 3X6 mm2 ውፍረት ያለው እና ጥራት ያለው Original cable መሆኑን አረጋግጠው የኤሌክትሪክ መኪና ሀይል መሙያ ቻርጀር ዘርጋታ ወይም Installation መስራትም ሆነ ማሰራት ይኖርብዎታል።
ለበለጠ መረጃ ይህንን ቪዲዮ ይመልከቱ፤
https://youtu.be/eZKNGVGHLaA?si=EQ7CBZmEdNhIPuQ8
አድራሻችን፡ ባምቢስ NOC ማደያ አጠገብ፣ 3ኛ ፎቅ፤ አዲስ አበባ
ስልክ ቁጥር፡ +251 988 88 88 04
Get in Touch
Phone Number
+251 963 00 0000
Phone Number
+251 964 00 0000
Phone Number
+251 969 00 0000
Email Address
info@markoncarimporter.com
+251 968 00 0000
Our Office
Addis Ababa, Ethiopia